የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለላቦራቶሪ ባለሙያዎች የጥራት አመራር ስልጠና መስጠቱ ተገለጸ።

የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም

የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከመንግስትና ከግል ጤና ተቋማት ለተውጣጡ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች በላቦራቶሪ ጥራት አመራር (Laboratory Quality Management system(LQMS)) ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።

ኢንስቲትዩቱ በክልሉ የሚሰጡ የላቦራቶሪ አገልግሎቶች ጥራታቸውን የጠበቁ፣ ትክክለኛና ተዓማኒ እንዲሆኑ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በተከታታይ እያጠናከረ መሆኑን ገልጿል።

የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ በመልዕክታቸው ፦ እየተከናወኑ ያሉ የጥራት ማሻሻያ መርሃ ግብሮች፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እና ተከታታይ የቴክኒክ ድጋፎች በመሆናቸው በርካታ የጤና ተቋማት ወደ ዓለም አቀፍ የላቦራቶሪ እውቅና (Accreditation) ደረጃ እየተሸጋገሩ ይገኛሉ።

በጥራት አመራር የተደገፈ የላቦራቶሪ አገልግሎት መኖሩ ትክክለኛ የምርመራ ውጤት ለማምጣት፣ የታካሚዎችን ህክምና ለማሻሻል እና በክልሉ ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኞችን በፍጥነት ለመለየትና ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል።

የስልጠናው ዋና ዓላማ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች የጥራት አመራር ሥርዓትን በተግባር እንዲተገብሩ፣ ትክክለኛና ተዓማኒ የምርመራ ውጤቶችን እንዲያመነጩ እንዲሁም የላቦራቶሪ አገልግሎትን ወደ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ማሸጋገር መሆኑ ተገልጿል።

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሰኔ 19/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- admin@sphi.gov.et

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *