እንኳን ደስ አለዎት!
ክብርት ደ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነዉ በድጋሚ ተሹመዋል!
ባለፉት አመታት በዓለም ደረጃ እንዲሁም በኢትዮዽያ የተከሰቱ እንደ ማርበርግ ቫይረስ ያሉ ወረርሽኞችን በመከላከልና በመቆጣር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ልምዳቸዉን በመጠቀም በኢትዮጵያ ጠንካራና ፈጣን ምላሽ ሰጪ የሆነ የጤና ስርዓት እንዲፈጠር በትጋት ሰርተዋል።
የተከበሩ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከ28/01/2019 ዓ.ም ጀምሮ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አቅራቢነት በኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነዉ በድጋሚ ተሹመዋል።
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት አመራርና መላዉ ሰራተኞች ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን በድጋሚ በመሾማቸዉ የተሰማንን ልባዊ ደስታ እንገልጸለን። ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ በቀጣይም ያለቸዉን ልምድና የአመራር ብቃት በመጠቀም በጤናዉ ዘርፍ የተያዙ ዋና ዋና ግቦችን ከግብ እንደሚያደርሱ ያለንን ሙሉ እምነት እየገለጽን መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸዉ እንመኛለን!
የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
መሰከረም 28/2019 ዓ/ም
ሀዋሳ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
![]()
![]()
![]()
ይመልከቱ
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173
Telegram: https://t.me/c/1865772308/1
Email:- admin@sphi.gov.et
See less







