እንኳን ደስ አለዎት!

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር መሳይ ሀይሉ የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በመሾማቸው የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማኔጅመንትና ሠራተኞች ልባዊ ደስታችንን እየገለጽን፣ ከልብ እንኳን ደስ አለዎት እንላለን።

ዶ/ር መሳይ በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሆነው በነበሩበት የአመራር ዘመን፣ የኢንስቲትዩቱን ተልዕኮ በማጠናከርና የሕብረተሰብ ጤና ሥራዎችን በማስፋፋት የማይዘነጋ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

በተለይም በሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከልና ምላሽ፣ በሕብረተሰብ ጤና ምርምር፣ በብሔራዊ የላብራቶሪ አቅም ግንባታ፣ በጤና መረጃ አስተዳደርና ትንተና፣ እንዲሁም በ‘አንድ ጤና’ (One Health) ዘርፎች የተቋሙን አቅም በማጠናከርና የሥራ ትስስርን በማሳደግ ለኢንስቲትዩቱ የእድገት ጉዞ ያበረከቱት አስተዋጽኦ በአክብሮት ይታወሳል።

ዛሬ የተሰጥዎት አዲሱ ኃላፊነት ደግሞ ያሎትን ልምድ፣ ዕውቀትና የአመራር አቅም በሌላ የሕዝብ አገልግሎት መስክ ለማበርከት የተሰጠ አዲስ የአገልግሎት ምዕራፍ ነው።

የSPHI ማኔጅመንትና ሠራተኞች በኢንስቲትዩቱ ለነበረዎት አመራርና አገልግሎት ከልብ እያመሰገንን፣ በአዲሱ ኃላፊነትዎ ለሲዳማ ክልልና ለሕዝቡ የላቀ ለውጥና ውጤት እንዲያመጡ ከልብ እንመኛለን።

እንኳን ደስ አለዎት!

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *