’የጤናው ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር ዕድገት” በሚል መሪ ቃል በክልሉ በሁሉም ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ከጤና ባለሙያዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።
መድረኩ ከለውጡ ወዲህ በዘርፉ የተገኙ ስኬታማ ድሎችን በመገምገም የተገኙ ውጤቶችን ለማዝለቅ በሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮችን ለመፍታት የዘርፉ ባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል ነው። የጤና ባለሙያ ከማንኛውም የተሳሳተ መረጃ እራሱን በማራቅ በዚህ ምክንያት በዜጎች ላይ የሚመጡ ጉዳቶችን በመገንዘብ በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሠራጩ የሀሰት መረጃዎች ሳይወናበድ የገባውን የሙያ ቃል ኪዳን እና መሐላ ጠብቆ ማኅበረሰቡን በቅንነት ማገልገል እንደሚገባ ተገልጿል፡፡…










