የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ በሽታን ለመቆጣጠርና ለማጥፋት የሚሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ ከተለያዩ የአሜርካ ዩኒቨርሲቲ ከተውጣጡ ሳይንቲስቶች ጋር ውይይት አደረገ፡፡
በወባ በሽታ ምርምር ዙሪያ የምርምር እቅድ ነድፈው ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩትን የምርምር ስራዎች ለመገምገም ከሶስት የአሜሪካ ዩንቬርሲቲዎች (University of North Carolina, Brown University እና Notre Dame University) የተውጣጡ ስድስት ከፍተኛ የምርምር ልኡካን ቡድን ከኢንቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እና ከኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸዉ ቶሌራ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የወባ…









