በዛሬው ዕለት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሰራተኞች እና የማኔጅመንት አባላት በኢንስቲትዩቱ የ2019 የመጀመሪያ ሩብ አመት ዕቅድ ክንውንና አሁን እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ላይ ውይይት አድርገዋል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይረክተር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ኢንስቲትዩቱ በ2019 በጀት አመት ዕቅድ ክንውን የላቀ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ጠቅሰው። ያለፈውን ጠንካራ ጎን አጠናክሮ በመቀጠል ለተጨማሪ አፈጻጸም ጠንክረን መስራት አለብን በማለት አሳስበዋል።

በስብሰባው የተገኙ የተቋሙ ሰራተኞች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት የተቋሙን መልካም አፈጻጸም በመቀጠል ከእነሱ የሚጠበቀውን ሁሉ በመፈጸም ከዚህም የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንችላለን ብለዋል።

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ጥቅምት 02/2019 ዓ/ም

ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- admin@sphi.gov.et

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *