በመደበኛው ክትባት ተደራሽ ያልሆኑ ህፃናትን በማካካሻ ፕሮግራም መከተብ ተችሏል

________

ሀገር አቀፍ የክትባት ፕሮግራም እና በክትባት መከላከል የሚቻሉ በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ የ9ወራት የአፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀምሯል።

በክትባት ተደራሽነት ዙሪያ በርካታ ስራዎች የተሰሩና አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ቢሆንም ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች አሁንም ክትባት ያልጀመሩ ሕፃናት አሉ ያሉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የተገኙ ስኬቶችና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በተመለከተ የመፍትሔ አቅጣጫዎች እንዲቀመጡ አሳስበዋል።

ባለፉት ዓመታት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ኮቪድ 19ን ጨምሮ ወረርሽኞችና ሰው ሰራሽ አደጋዎች እንዳጋጠሟቸው የጠቀሱት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሃይሉ በበኩላቸው በተሰሩ ስራዎች ወረርሽኞች መቀነሳቸውን እንዲሁም በመደበኛው ክትባት ተደራሽ ያልሆኑ ህፃናትን በማካካሻ ፕሮግራም መከተብ መቻሉን ገልፀዋል፣ መድረኩ በቀጣይ ቀናትም ይካሄዳል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *