የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በቲቢ ማይክሮስኮፒ ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ።
የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም
የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከተለያዩ የጤና ተቋማት ለተውጣጡ 63 የላቦራቶሪ ባለሙያዎች በቲቢ ማይክሮስኮፒ (TB Microscopy) ምርመራ ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከReach Ethiopia Urban TB Lon II project ጋር በመተባበር በሁለት ዙር ሰጠ።
ስልጠናው በክልሉ የቲቢ ምርመራ ጥራትን በማሻሻል በሽታውን በቀድሞ ለመለየትና ስርጭቱን ለመቀነስ ያለመ ነው።
የኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ እንደገለጹት፣ በተከታታይ የሚሰጡ ስልጠናዎችና የክትትል ሥራዎች ምክንያት በክልሉ የላቦራቶሪ አገልግሎት ጥራት እየተሻሻለ ሲሆን፣ ይህ ስልጠናም ትክክለኛ የAFB ማይክሮስኮፒ ምርመራና የጥራት ቁጥጥር አሠራርን የበለጠ ለማጠናከር ያግዛል።
ስልጠናውን ያጠናቀቁት ባለሙያዎች ወደ ተቋማቸው በመመለስ ያገኙትን ዕውቀት በሥራ ላይ በማዋል፣ ለባልደረቦቻቸው በማስተላለፍ፣ የላቦራቶሪ ጥራት ስርዓትን በማጠናከርና የቲቢ ምርመራ ውጤቶችን በአግባቡ በመመዝገብ ለክልሉ የቲቢ ቁጥጥር መርሃ ግብር የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተጠቁሟል።
የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 11/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
![]()
![]()
![]()
ይመልከቱ
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173
Telegram: https://t.me/c/1865772308/1
Email:- admin@sphi.gov.et
See less






















