በሲዳማ ክልል የወባ በሽታ ስርጭትን ለመግታት ህዝባዊ ንቅናቄ ለመፍጠር ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ
የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ግንቦት 29/2018 ዓ.ም
በሲዳማ ክልል እየታየ የመጣውን የወባ በሽታ ስርጭት በዘላቂነት ለመግታት፣ ለመቆጣጠርና የቅድመ መከላከል ሥራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ::
ሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ በመልዕክታቸው የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በክልሉ ውስጥ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሆኖም የአየር ንብረት ለውጥ በክልሉ የወባ በሽታ ስርጭትን እያስፋፋ በመምጣቱ በሽታውን ለመግታት የተቀናጀ ርብርብ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
አቶ በላይነህ በንግግራቸው ኢትዮጵያ በ2030 ወባን ለማጥፋት ያስቀመጠችውን ብሔራዊ ግብ ለማሳካት የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ ወባ ለህብረተሰቡ የጤናና የልማት እንቅፋት እንዳይሆን የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ሥራዎች በሰፊው ሊጠናከሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በክልሉ ከፍተኛ የወባ ሥርጭት አለባቸው ተብለው በተለዩ 15 ወረዳዎችና በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የወባ መከላከልና ቁጥጥር ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ መላው ኅብረተሰብ፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሚዲያ ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ሚና በንቃት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደስታ ዶጊሶ በበኩላቸው፣ የመድረኩ ዋና ዓላማ በህብረተሰቡ ዘንድ ሰፊ ንቅናቄ በመፍጠር የወባ በሽታን በተቀናጀ መንገድ መከላከል መሆኑን ገልጸዋል።
ወባን ለመቆጣጠር በጤናው ዘርፍ ብቻ የሚደረግ ጥረት በቂ እንዳልሆነ የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮች፣ የማህበረሰብ መሪዎች፣ ሃይማኖት ተቋማትና ህብረተሰቡ በትብብርና በቅንጅት ከሰሩ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡
ዳይሬክተሩ እንዳሉት፣ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና በወባ መከላከል ሥራዎች ውስጥ ተሳትፎውን ለማጠናከር የተለያዩ የተግባቦትና የማንቃት ሥራዎች እየተከናወኑና ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። ወባን ለመከላከል ማህበረሰቡን ማሳተፍ፣ ማስተሳሰርና ባለቤትነት እንዲወስድ ማድረግ የላቀ ሚና እንዳለውም አክለዋል።
በመድረኩ ላይ የክልሉ የወባ በሽታ አሁናዊ ሁኔታ፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ ያለው የበሽታ ስርጭት፣ ለወባ ተጋላጭነት መንስኤዎች፣ የቤት ውስጥ የጸረ-ወባ ኬሚካል እርጭት (IRS) ዘመቻ ዝግጁነት እንዲሁም የወባ ማጥፊያ መድኃኒቶችና የበሽታ መመርመሪያ መሣሪያዎች አቅርቦትን በተመለከተ ሰነዶች ቀርበዋል፡፡
በውይይቱም የወባ በሽታ መከላከል ሥራን ለማጠናከር የማህበረሰብ ተሳትፎና የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ በቀረቡ አጀንዳዎች ዙሪያ በተደረገው ሰፊ ውይይት ተገልጿል፡፡
ወባን መከላከል የሁላችንም ኃላፊነት ነው፤ የአካባቢ ንጽህናን እንጠብቅ፣ አጎበሮችን ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ እንጠቀም፣ ያቆሩ ውሃዎችን እናስወግድ፤ በጋራ በመረባረብ ከወባ የጸዳ ማህበረሰብ እንገንባ” ሲሉም አሳስበዋል።
በመጨረሻም በመድረኩ ላይ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት፣ የቢሮው ተጠሪ ተቋማት፣ከከተማ አስተዳደር፣ ከዞን ጤና ዴስኮች፣ የወባ ጫና ከፍተኛ ከሆነባቸው ወረዳዎች የስራ ኃላፊዎች ፣ ሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሚዲያ አካላት እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
29/09/2018 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
![]()
![]()
![]()
ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:




Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
YouTube:
Tik Tok:
See less






