የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለሀዋሳ ደም ባንክ ሠራተኞች በGood Manufacturing Practice (GMP) ላይ ስልጠና ሰጠ።
የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም
የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለሐዋሳ ደም ባንክ ሠራተኞች በመልካም የማምረት አተገባበር (Good Manufacturing Practice–GMP) ላይ ስልጠና ሰጥቷል።
የስልጠናውን መርሃ ግብር ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ በንግግራቸው ፣ እንዲህ ያሉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የደም ባንኩን የአገልግሎት ጥራትና ደህንነትን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸው ፤ የደም ባንኩ ሠራተኞችም ከስልጠናው የሚያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በዕለት ተዕለት ሥራቸው በመተግበር ደምና የደም ተዋፅኦዎች የሚፈለገውን የጥራት መስፈርት እንዲያሟሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የሀዋሳ ደም ባንክ አስተባባሪ አቶ ዘመዴ አራርሳ እና የኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ በበኩላቸው ለተሳታፊዎችን መልዕክት አስተላልፈዋል።
ስልጠናው የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መስፈርቶችን ያሟላ ደምና የደም ተዋፅኦዎች የሚፈለገውን የጥራት፣ የደህንነትና የውጤታማነት መስፈርት ሊያያሟሉ የሚያስችሉ የሥራ ሂደቶችና የአሠራር ሥርዓቶችን መሠረት ያደረገ በመሆኑ የተጠቃሚዎችን ደህንነት የሚያስጠብቅ መሆኑ ተገልጿል ።
በተጨማሪም ለደም ተዋፅኦ ዝግጅት የሚያስፈልገውን 450 ሚሊ ሊትር የደም መጠን በአግባቡ ስለመሰብሰብ እንዲሁም የደም ለጋሾችን ደህንነት (Blood Donor Vigilance) በመከታተል ሥርዓት ዙሪያ ተግባራዊና በቂ ስልጠና ተሰጥቷል።
የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሐምሌ 1/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
![]()
![]()
![]()
ይመልከቱ
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173
Telegram: https://t.me/c/1865772308/1
Email:- admin@sphi.gov.et
See less


























