የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የአደጋዎች ቁጥጥር ስርዓትን የሚያዘምን ዲጂታል አሰራር ይፋ ሆነ
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ስርዓትን የሚያዘምን ዲጂታል አሰራር ይፋ አድርጓል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በማስተዋወቂያ መድረኩ ላይ እንዳሉት÷ የዲጂታል ስርዓቱ በኢትዮጵያ በእያንዳንዱ ወረዳ ምን አይነት የጤና ችግር አለ የሚለውን ለመለየት ያስችላል። ስርዓቱ በፊት የነበረውን የተበታተነ የመረጃ አያያዝ የሚያስቀር መሆኑን ገልጸው÷ ይህም በየደረጃው የጤና መረጃ ልውውጥ እንዲሳለጥ ያግዛል ብለዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ…










