በሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 10ኛው የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ፎረም ተሳታፊዎች ከውይይቱ ጎን ለጎን በክልሉ ውስጥ የተሰሩ ለተሞክሮ የሚሆኑ ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
ከተጎበኙት ተቋማት መካከል በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው የሚሊኒየም ጤ/አ/ጣቢያ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ሥራ እየተመራ ያለበትን አሠራር ፣ በኢንስቲትዩቱ የድጂታል ላይብራሪ እና በመስሪያ ቤቱ ህንጻ ላይ እየተተገበረ የሚገኘው የጽዱ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ይገኙበታል። ከ20 በላይ የሚሆኑ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትን እና ሌሎች ከየክልል ቢሮዎች እንዲሁም ከፌደራል መ/ቤቶች የተወጣጡ ተሳታፊዎችን ያካተተው ጉብኝት ላይ የነበሩ እንግዶች…










