
Similar Posts

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ በሽታን ለመቆጣጠርና ለማጥፋት የሚሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ ከተለያዩ የአሜርካ ዩኒቨርሲቲ ከተውጣጡ ሳይንቲስቶች ጋር ውይይት አደረገ፡፡
Byadminበወባ በሽታ ምርምር ዙሪያ የምርምር እቅድ ነድፈው ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩትን የምርምር ስራዎች ለመገምገም ከሶስት የአሜሪካ ዩንቬርሲቲዎች (University of North Carolina, Brown University እና Notre Dame University) የተውጣጡ ስድስት ከፍተኛ የምርምር ልኡካን ቡድን ከኢንቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እና ከኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸዉ ቶሌራ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የወባ…

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት የጤና አጋሮችንና የየደረጃውን የሴክተሩን አካላት ያሳተፈ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
Byadminበመድረኩ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ባስተላለፉት መልዕክት :- በክልሉ ባለፉት ጊዜያት በተሰራው ስራ የተሻለ ውጤት በሴክተሩ እንደተመዘገበ ጠቁመው ለስኬቱ ካበቁን አሠራሮች አንጻር ኃላፊዋ ሲገልጹ በክልሉ የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ አጋሮች እና የየደረጃው የጤና ሰክተር ተዋናዮች ቅንጅታዊ አሠራር መሆኑን ገልጸዋል ። ኃላፊዋ አክለውም የመጣው ውጤት ከመዋቅር መዋቅር ልዩነት ያለው መሆኑንም አልሸሸጉም ። ከጉድለቶቹ…

ለጤና ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ የሚሰጡ ቡድኖችን ማጠናከር እና መጠቀም ላይ ስልጠና ተጀምሯል።
Byadminየኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ በሀዋሳ ከተማ ለ100 ሁለገብ ባለሙያዎች የአንድ ወር ስልጠና ከፈቱ። ስልጠናው በ24 – 48 ሰአታት ውስጥ በድንገተኛ አደጋዎች ለመሰማራት ዝግጁ የሆኑ በደንብ የሰለጠኑ፣ የታጠቁ፣ ቀልጣፋ እና ተለዋዋጭ ባለሙያዎችን ዝርዝር በማዘጋጀት ለጤና ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት ምላሽ ሰጪ ቡድኖችን ማጠናከር እና መጠቀም ላይ ያተኩራል። ስልጠናው የኢፒአይአይ ከጤና ጥበቃ…

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ቡድን የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቢሮና ላቦራቶሪን ጎበኙ ።
Byadminበሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ በክብርት ፋንታዬ ከበደ የሚመራው የቋሚ ኮሚቴዎች ቡድን በክልሉ በተለያዩ ዞኖች ጉብኝት ያካሄደ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በክልሉን ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ አገልግሎት አሰጣጡና በሀገራችን 4ኛ የሆነው የጂኖሚክስና ባዮኢንፎርማቲክስ ማዕከል ትግበራ ያለበትን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል። የቋሚ ኮሚቴ ቡድኑ በጉብኝቱ የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ የበሽታዎች ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ስርዓቱን አጠናክሮ እየሰራ ያለ…

እንኳን ደስ አለን!
Byadminኢንስቲትዩታችን በሚሰጠው የላቦራቶሪ አገልግሎት የአለም አቀፍ ስታንዳርድ(ISO 15189:2022) ማስቀጠሉ ተረጋግጦ የአክሬዲተሽን ሰርተፍኬት ከኢትዮጵያ አክሬዲተሽን አገልግሎት ተበርክቶልናል። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ግንቦት 09/2018 ዓ/ም ሀዋሳ ለተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት: ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794 Web site: sphi.gov.et/emergency See less

በማርበርግ ቫይረስ በሽታ መከላከል ላይ ያተኮረ አውደ-ጥናት ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ተካሄደ
Byadmin_____________ መድረኩ የተዘጋጀው በማርበርግ በሽታ ዙሪያ አሁን ያለውን ሁኔታ ለመግለጽ እና የሃማኖት ተቋማት እንዴት በሽታውን መከላከል እንደሚቻል ግንዛቤን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ የገለጹ ሲሆን፤ ለታማሚዎች በመጸለይ እንዲሁም ታክመው የዳኑ ሰዎች ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ድጋፍ እንዲያደርጉም መልአክት አስታልፈዋል፡፡ በተጨማሪም የተሳሳተ መረጃን ለማጥራት የሃይማኖት ተቋማት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አክለዋል፡፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት…
