የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የተመሠረተበትን 100ኛ ዓመት ( Centenary) ክብረ በዓል አስመልክቶ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ ።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሐምሌ 7/2018 ዓ.ም
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት አመራሮችና አጠቃላይ ሠራተኞች ፦ የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ጉልህ አሰተዋጽኦ ላስመዘገበው ለኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት (EPHI) ለመቶኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ / እንኳን ደስ አላችሁ!!
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ባለፉት 100 ዓመታት የተጓዘበት ረጅም ምዕራፍ ፤ የሀገራችንን ሕብረተሰብ ከወርሸኝ ለመጠበቅ፣ የህብረተሰቡን የጤና ችግር በምርምር በመፍታት፣ ወረርሽኞች ሲከሰቱ የወረርሽኞችን መንስኤ በላቀ የላቦራቶሪ ምርመራ በማረጋገጥ ያበረከተው አሰተዋጽኦ ታሪካዊ ነው።
ይህ የመቶ ዓመት ታሪካዊው ጉዞ የተቋሙን ተልዕኮ ክንውን ፣ የህዝባችንን ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትና ብሔራዊ የጤና ደህንነትን ማረጋገጥ እና ዘመናዊ ቴክኒዎሎጂዎችን ተግባራዊ ማድረግ ዋና ዋናዎቹ የኢንስቲትዩቱ ስኬት ናቸው ።
ስለሆነም መላው የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት አመራሮች ፣ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ዊንግ ባለሙያዎች ፣ ተመራማሪዎች ፣የላቦራቶሪ ባለሙያዎች ፣የብሔራዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ባለሙያዎችና የድጋፍ ሠራተኞች በሙሉ:-እንኳን ለ100ኛ ዓመት ክብረ-በዓል አደረሳችሁ !
ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል
የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 7/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
![]()
![]()
![]()
ይመልከቱ
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173
Telegram: https://t.me/c/1865772308/1
Email:- admin@sphi.gov.et
See less







