የካውንት ዳውን 2030 ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል
———————- የዘላቂ ልማት ግቦችን (Sustainable Development Goals 2030 /SDG/) መነሻ በማድረግ በመላው አፍሪካ የሚገኙ የጤና መረጃዎችን፣ የእናቶች እና የህፃናት ጤና አፈጻጸምን ለመገምገም የተዘጋጀው “ካውንትዳውን 2030” (Countdown 2030) የተሰኘው አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ከ36 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የጤና ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣ የፖሊሲ አውጪዎች፣ ተመራማሪዎች እና የአለም አቀፍ…




